መከላከያ የተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈረመ

ጦሮቹ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረው ተስፈኛ ተጫዋችን በመጨረሻው ሰዓት የግላቸው አድርገዋል።
እስካሁን ድረስ የሁለት አዲስ ተጫዋቾች ዝውውር አከናውነው የነባር ተጫዋቾች ውል ለማራዘም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት መከላከያዎች የለገጣፎ ለገዳዲው ተከላካይ ነስረዲን ኃይሉን አስፈርመዋል። ከዚህ ቀደም በቡራዩ ከተማ ቆይታ የነበረው እና እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለመግባት ፉክክር ውስጥ ለነበረው ለገጣፎ ለገዳዲ የተሳካ ጊዜ የነበረው ተከላካዩ ባለፈው ዓመት በፕሪምየር ሊጉ ከ50 ጎሎች በላይ ጎሎች ተቆጥረውበት የነበረው የጦሩ ተከላካይ መስመርን ለማጠናከር ጥሩ ግዢ እንደሆነ ይገመታል።

እስካሁን ድረስ በቡድኑ የመከላከል ዙርያ ላይ ዝውውሮች የፈፀሙት መከላከያዎች በቀጣይም አዳዲስ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነባሮችም ውል ለማራዘም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡