ቻምፒየንስ ሊግ| ያሬድ ከበደ ከወሳኙ ጨዋታ ውጭ ሆነ

የምዓም አናብስቱ አማካይ በወሳኙ የቻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ እንደማይሰለፍ ተረጋግጧል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በወጥ ብቃት መቐለን ያገለገለው እና ባለፈው የውድድር ዓመት ቡድኑ ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉት ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሰው ሁለገቡ ተጫዋች ላለፉት ሰባት ቀናት ልምምድ እንዳልሰራ ሲታወቅ ከወሳኙ ጨዋታ ውጭ መሆኑም ተረጋግጧል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ አጨዋወት ላይ ይበልጥ ጎልቶ የወጣው ተጫዋቹ ከካኖ ስፖርት አካዳሚ ጋር በተደረገው የመጀመርያው ዙር የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጎ በርካታ የግብ ዕድሎችም መፍጠር ችሎ የነበረ ሲሆን ከጉዳቱ አገግሞ መቼ እንደሚመለስ ባይረጋገጥም በቀጣይ ሳምንት ወደ ልምምድ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡