የአስቻለው ታመነ ቀጣይ ማረፍያ የት ይሆናል?

የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ አስቻለው ታመነ ቀጣይ ማረፍያ በቅርቡ ይለያል።

ባለፉት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ስኬት ውስጥ ስሙ በቅድሚያ የሚጠቀሰው ይህ የተከላካይ ክፍል ተጫዋች ባለፉት ቀናት ከወልቂጤ ከተማዎች ጋር ንግግር ማድረጉ ሲታወቅ አዲስ አዳጊዎቹን የመቀላቀል ዕድል ሊኖረው እንደሚችልም ታውቋል። እስካሁን ድረስ ከፈረሰኞቹ ጋር ውሉን ያላራዘመው ተከላካዩ ከወልቂጤ የተሻለ ጥቅማ ጥቅም እንደቀረበት ሲረጋገጥ ክለቡም የተጫዋቹን ምላሽ እየጠበቀ እንደሚገኝ ታውቋል።

በ2007 ክረምት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካመራ በኋላ ሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች መሆን የቻለው ተጫዋቹ እስከ ቀጣይ ሳምንት ድረስ ከፈረሰኞቹ ጋር የመቆየቱ ወይም አዲስ አዳጊዎቹን የመቀላቀሉ ጉዳይ ይለይለታል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡