ቴዎድሮስ ታፈሰ በመከላከያ ይቆያል

ከመከላከያ ታዳጊ ቡድን አድጎ ላለፉት ዓመታት ዋናው ቡድንን በቋሚነት ያገለገለው ቴዎድሮስ ታፈሰ ከክለቡ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።

ተጫዋቹ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሊጉ ላይ ከታዩ ምርጥ የጥልቅ አማካይ ክፍል ተጫዋቾች ግንባር ቀደሙ የነበረ ሲሆን በርከት ያሉ ክለቦች ሊያስፈርሙት እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ምርጫውን በጦሩ ቤት መሰንበት አድርጓል። ከነባሮቹ የቡድኑ ተጫዋቾች ውሉን ያራዘመ የመጀመርያው ተጫዋችም ሆኗል።

ምንተስኖት አሎን በማስፈረም ወደ ተጫዋቾች ዝውውር ገበያ የገቡት ጦሮቹ በቀጣይ ቀናት የነባር ተጫዋቾች ውል ያራዝማሉ ተብሎ ሲጠበቅ ትላልቅ ዝውውሮች ይፈፅማሉም ተብሎ ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡