ኢትዮጵያዊ ዳኞች የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ለመምራት ወደ ሱዳን ያመራሉ

በሱዳኑ ኤል ሜሪክ እና የአልጀሪያው ጂኤስ ካቢሌ መካከል የሚደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በኢትዮጵያዊ ዳኞች ይመራል።

ቅዳሜ ኦምዱርማን ላይ የሚደረገውን ይህን ጨዋታ በላይ ታደሰ በዋና ዳኝነት እንዲመራ ሲመደብ ክንዴ ሙሴ እና ክንፈ ይልማ በረዳትነት ተሰይመዋል። አራተኛ ዳኛ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ወደ ጅቡቲ አምርቶ የነበረው ቴዎድሮስ ምትኩ እንዲሆን ተመርጧል።

የሁለቱ ቡድኖች የመጀመርያ ጨዋታ ኦገስት 9 ካቢሌ ላይ ተደርጎ ጄኤስ ካቢሌ 1-0 ማሸነፍ ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡