ፓትሪክ ማታሲ ሃገሩን ለመወከል ጥሪ ደርሶታል

ኬንያዊው የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታሲ ሃገሩን ለመወከል ጥሪ ደርሶታል።

በዓመቱ መጀመርያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተቀላቅሎ ከፈረሰኞቹ ጋር መልካም የሚባል ቆይታ የነበረው እና ግብፅ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በግሉ ምርጥ ጊዜ ያሳለፈው የ31 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ሃገሩ ኬንያ ከዩጋንዳ ጋር ለምታደርገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነው ከአዲሱ አሰልጣኝ ጥሪ የደረሰው።

የሃገሩ እግር ኳስ አፍቃሪያን ፊት የነፈጋቸው ሰባስትያን ሚኜን በማሰናበት ወጣቱ የ43 ዓመቱ ኬንያዊ አሰልጣኝ ፍራንሲስ ኪማንዚን የቀጠሩት ኬንያዎች በቀጣይ ላላቸው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሌሎች ተጨማሪ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች እንደሚያደርጉም ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡