መከላከያ የመጀመርያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ምንተስኖት አሎ የጦሮቹ ማልያ ለብሶ ለመጫወት ፊርማው ያኖረ የመጀመርያው ተጫዋች ሆኗል።

ዘላለም ሽፈራውን ዋና አሰልጣኝ አድርገው በመቅጠር ወደ ዝውውር ገበያው የገቡት መከላከያዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረው ግብ ጠባቂው ምንተስኖት አሎን አስፈርመዋል። ከዚ በፊት በሰበታ ከተማ እና ፋሲል ከነማ መጫወት የቻለው ተስፈኛው ግብጠባቂ ባለፈው ዓመት የቋሚነት ቦታው በሃሪሰን ሄሱ ቢነጠቅም የጣና ሞገዶቹ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድጉ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ነው።

በዓመቱ መጀመርያ ለኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድን መሰለፍ የጀመረውና በቻን ማጣርያም ተመራጭ የነበረው ተጫዋቹ በቀጣይ ሳምንት ሌሶቶን በሚገጥመው ስብስብ መካተቱም ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡