ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች| ሩዋንዳ ማለፏን ስታረጋግጥ ሁለተኛው ጨዋታ ተቋርጧል

በኤርትራ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው እና ስምንተኛ ቀኑ የያዘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬም ሲቀጥል ሩዋንዳ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። የደቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳ ጨዋታ ደግሞ ተቋርጧል።

ስምንት ሰዓት ላይ የጀመረው እና ተመጣጣኝ ፉክክር ታይቶበታል የተባለው የሩዋንዳ እና የታንዛንያ ጨዋታ ሲሆን በጨዋታውም ሩዋንዳ ተጋጣሚዋን 2-1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።

10:30 የተጀመረው የዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ጨዋታ ደግሞ እስከ ዕረፍት ዩጋንዳ አምስት ለ ባዶ እየመራች ወደ ዕረፍት ቢያመሩም ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ ብዙይ ሳይሄድ ከጨዋታው በፊት አምስት ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት በማጧቷ በጎዶሎ ቅያሪ ወደ ጨዋታው የገባችው ደቡብ ሱዳን በሁለተኛው አጋማሽ ተጨማሪ አምስት ተጫዋቾች በጉዳት በማጧቷ ጨዋታው በአስገዳጅ ሁኔታ ተቋርጧል፤ ዩጋንዳም የጨዋታው አሸናፊ ሆናለች። ከሩዋንዳ በመቀጠል ወደ ግማሽ ፍፃሜው የተሸጋገረች ሌላዋ ቡድንም ሆናለች።

# ቡድን | ተጫ | ልዩነት | ነጥብ
1 ዩጋንዳ 3 (+10) 9
2 ሩዋንዳ 3 (+7) 9
3 ታንዛኒያ 3 (+3) 3
4 ኢትዮጵያ 3 (-6) 1
5 ደ/ሱዳን 4 (-14) 1

ቀጣይ ጨዋታዎች ነገ ሲቀጥሉ በምድብ ሀ የመጨረሻ ጨዋታዎች 8:00 ላይ ብሩንዲ ከ ሱዳን፣ 10:30 ላይ ሶማሊያ ከኤርትራ ይጫወታሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡