ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች| ኢትዮጵያ በታንዛንያ ስትሸነፍ ዩጋንዳ ሩዋንዳን አሸንፋለች

በኤርትራ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዛሬም ሲቀጥል ኢትዮጵያ በታንዛንያ ሶስት ለአንድ ስትሸነፍ ዩጋንዳም ሩዋንዳን ሶስት ለባዶ አሸንፋለች።

ዛሬ የተካሄዱት ሁለት የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ሲሆኑ ቀዳሚ የነበረውም የኢትዮጵያ እና የታንዛንያ ሲሆን በጨዋታውም ታንዛንያ ሶስት ለአንድ አሸንፋለች። ቀጥሎ የተካሄደው እና ኢትዮጵያዊው ዳኛ ለሚ ንጉሴ የተሳተፈበት የጠንካራዋ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ ጨዋታ ሲሆን ዩጋንዳ ከሙሉ ብልጫ ጋር ሶስት ለባዶ አሸንፋለች።

በውድድሩ ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ አራት ቡድኖች የተለዩ ሲሆን ዩጋንዳ ፣ ኬንያ ፣ ብሩንዲ እና ኬንያም የግማሽ ፍፃሜው ተፋላሚዎች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡