መከላከያ ሁለተኛ ተጫዋች አስፈረመ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ምንተስኖት አሎን ከባህር ዳር ከተማ ያስፈረሙት መከላከያዎች አሁንም ባለፈው ዓመት ከጣና ሞገዶች ጥሩ ዓመት ያሳለፈው አስናቀ ሞገስ አስፈርመዋል።

ከዚ በፊት በሁለት አጋጣሚዎች በባህር ዳር ከተማ ቆይታ የነበረው እና በኢትዮጵያ ቡና መጫወት የቻለው ተጫዋቹ ባለፈው ዓመት መጀመርያ ዙር ጥሩ የተከላካይ ክፍል ከነበራቸው የጣና ሞገዶች ጥሩ ቆይታ የነበረው ሲሆን በማጥቃት ላይ ባለው ሚናም ይታወቃል። ተጫዋቹ የዝውውር መስኮቱ ከመከፈቱ በፊት ለአዳማ ከተማ ለመጫወት ከስምምነት ደርሶ የነበረ ቢሆንም ፊርማውን ባለማኖሩ ወደ ጦሩ ቤት አምርቷል።

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ዋና አሰልጣኝ አድርገው የቀጠሩት ጦሮቹ በቀጣይ ቀናት የነባር ተጫዋቾች ውል ያራዝማሉ ተብሎ ሲጠበቅ የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውርም ይፈፅማሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡