ሐብታሙ ወልዴ መከላከያን ተቀላቀለ

ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ተስማምቶ የነበረው ሐብታሙ ወልዴ ዝውውሩ ባለመሳካቱ ለመከላከያ ፌርማው አኖረ።

ባለፈው ወር መጨረሻ ሐብታሙ ወልዴ አዳማ ከተማን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ መስማማቱን መግለፃችን ይታወሳል። ሆኖም ዝውውሩ ፌደሬሽን ሄዶ ባለመፅደቁ እና በጊዜው መጠናቀቅ የነበረባቸው ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው ተጫዋቹ ለመከላከያ ፊርማውን አኑሯል።

በኢትዮጵያ መድን እና በድሬዳዋ ከተማ ጥሩ ቆይታ የነበረው፤ በመስመርና በዋና አጥቂነት መጫወት የሚችለው ተጫዋቹ የመከላከያ አራተኛ ፈራሚ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡