ወልቂጤ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች አስፈረመ

አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ አንድ ግብ ጠባቂ እና አማካይ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

ኤፍሬም ዘካርያስ ወልቂጤን ከተቀላቀሉት መካከል ነው። በመተሀራ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ የተጫወተው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ኤፍሬም የሁለት ዓመት የአዳማ ቆይታውን አጠናቆ ወደ አዲስ አዳጊው አምርቷል።

ጆርጅ ደስታ ሌላው ክለቡን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። ወጣቱ ግብ ጠባቂ በኢትዮጵያ መድን ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን ውስጥም ታቅፎ እንደነበር የሚታወስ ነው። ጆርጅ ውሉን ካራዘመው ቤሌንጌ እና አዲስ ከመጣው ይድነቃቸው ጋር ለቋሚነት ይፎካከራል።

ወልቂጤ እስካሁን 14 አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ቡድኑን በአዲስ መልክ ገንብቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡