ከኢትዮጵያ ቡና የለቀቀው ግብ ጠባቂ ወደ ኬንያ አምርቷል

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ቡናን ግብ ሲጠብቅ የነበረው ኢስማኤል ዋቴንጋ የኬንያው ክለብ ሶፋፓካን ተቀላቅሏል፡፡

የዩጋንዳው ቫይፐርስን ለቆ በዓመቱ መጀመርያ ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት ዓመት ውል የተቀላቀለው የ25 አመት ግብ ጠባቂ በሊጉ ዝቅተኛ ጎል ካስተናገዱ ግብ ጠባቂዎች መካከል አንዱ የነበረ ቢሆንም በተለይ በሁለተኛው የውድድር ዘመን አጋማሽ በጉዳት ከሜዳ ርቆ ቆይቷል።

ከዚህ ቀደም የሴካፋ ኮከብ ጎል ጠባቂ ሆኖ የተሸለመው ዋቴንጋ ከክለቡ ጋር በጋራ ስምምነት ከተለያየ በኋላ ወደ ኬንያ አምርቶ በሦስት ዓመታት ውል ሶፋፓካን መቀላቀል ችሏል።

በውድድር ዘመኑ ኢትዮጵያ ቡና ሲጠቀምባቸው የነበሩት የውጪ ዜጎች ሱሌይማን ሎክዋ፣ ኢስማኤል ዋቴንጋ፣ ዴኮ ሾሌ፣ አልሀሰን ካሉሻ እና ክሪዚስቶም ንታምቢ በአሁኑ ሰዓት ከቡድኑ ጋር አይገኙም።


© ሶከር ኢትዮጵያ