ስሑል ሽረ አምስተኛ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል

ሌሎች ክለቦች እና ከዐምናው እንቅስቃሴያቸው አንፃር በዝውውሩ ብዙም ተሳትፎ ያላደረጉት ስሑል ሽረዎች ዐወት ገብረሚካኤልን አስፈርመዋል።

በ2004 ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ቡድን አድጎ እስካለፈው ዓመት ድረስ በዋናው ቡድን የተጫወተው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዐወት ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደውን ክለብ ለቆ ወደ ጅማ አባጅፋር በማቅናት ከቡድኑ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት ነው ስሑል ሽረዎችን የተቀላቀለው።

ከዚህ ቀደም የአራት ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቀቁት ስሑል ሽረዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችን ለማስፈረምም ተቃርበዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ