ኦኪኪ አፎላቢ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አቅንቷል

ከአፍሪካ ውድድር በጊዜ የተሰናበቱት መቐለ 70 እንደርታዎች ናይጀርያዊው አጥቂን ማስፈረማቸውን በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።

ባለፈው ዓመት ካልተሳካው የኢስማዒልያ ቆይታው በኋላ አጋማሽ ላይ ወደ ጅማ አባጅፋር በድጋሚ በመመለስ ከክለቡ ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረው አጥቂው በክረምቱ የመቐለ ሶስተኛ ፈራሚ ሆኗል።

ጅማ አባ ጅፋር በ2010 የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ሲያነሳ በ23 ጎሎች የሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ የነበረው አጥቂው በድጋሚ ከቀድሞ አሰልጣኙ ገብረመድህን ኃይሌ ጋር የሚገናኝ ሲሆን በአማኑኤል ገብረሚካኤል ላይ ለተመሰረተው የመቐለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ተጨማሪ ኃይል እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

መቐለ በክረምቱ ከኦኪኪ ቀደም ብሎ ኤፍሬም አሻሞ፣ አልሀሰን ካሉሻ እና ታፈሰ ሰርካን ማስፈረሙ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ