ስሑል ሽረዎች ሰባተኛ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል

በዛሬው ዕለት ዲዲዬ ለብሪን ያስፈረሙት ስሑል ሽረዎች ጋናዊው መሐመድ ዓብዱልለጢፍን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

ጋናዊው የ29 ዓመት አማካይ በ2010 የውድድር ዓመት የሲዳማ ቡናን ማልያ ለብሶ መጫወት የቻለ ሲሆን በዛምብያው ሉሳካ ዳይናሞስ፣ በጋቦኑ ሲኤፍ ሞናና እና በጋናው አሻንቲ ጎልድ መጫወት ችሏል። ለዋናው የጋና ብሔራዊ ቡድንም በአምስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፏል።

አብዱለጢፍ በግራ መስመር ላይ ከተከላካይነት እስከ አጥቂነት መሰለፍ የሚችል ተጫዋች ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ