ኢትዮ ኤሌክትሪክ የተገቢነት ጥያቄ አቀረበ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን በ24 ቡድኖች እና በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በማዋቀሩ እኛን ማካተት ይገባዋል ሲል ለፌዴሬሽኑ በደብዳቤ አቤቱታውን አቀረበ።

እንደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጥያቄ ከሆነ 24 እንዲሆን በታሰበው አዲሱ የውድድር ፎርማት ከፍተኛ ሊግ እንዲገቡ የታሰቡትን ቡድኖች ሳይጨምር የ19 የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች የተካቱበት (የተገቢነት ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ) በከፍተኛ ሊግ በሁለቱም ምድብ ከአንድ እስከ አራት የወጡ ቡድኖችን በማካተት የተወዳዳሪ ክለቦች ቁጥር ወደ በ28 ከፍ እንዲል እና ኢትዮ ኤሌትሪክ በዚህ ውድድር ውስጥ እንዲገባ የሚል ጥያቄ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ለፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

ጉዳዩን የተመለከተው ሊግ ኮሚቴም የኢትዮ ኤሌክትሪክ የክለብ አመራሮችን በመጥራት ጥያቄውን እንደማይቀበለው ለክለቡ አሳውቋል። ይህ የሊግ ኮሚቴ ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ጉዳያችንን አጢኖ የመፍቴሄ ውሳኔ ይስጠን ሲሉ ሁለተኛ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስገብተዋል። በደብዳቤው መሠረትም እስከ ነገ ድረስ ለጥያቄያችን ተገቢውን ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ክለቡ በቅርቡ አቋሙን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

የጳጉሜ 6 እና መስከረም 5 ደብዳቤዎች ይህንን ይመስላሉ፡-


© ሶከር ኢትዮጵያ