ሀዋሳ ከተማ አምስተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

በዝውውሩ መዘግየት ታይቶባቸው የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች በዛሬው ዕለት አጥቂው የተሻ ግዛውን አስፈርመዋል፡፡

የሦስት የውጪ ተጫዋቾችን ጨምሮ የስድስት ነባሮችን ውል ያደሰው ክለቡ እስካሁን ሄኖክ አየለ፣ አለልኝ አዘነ፣ ዘላለም ኢሳይያስ እና ሀብቴ ከድርን ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ በአጥቂ እና አማካይ ስፍራ ላይ መጫወት የሚችለው የተሻ ግዛውን በሁለት ዓመታት ውል አስፈርመዋል፡፡

የቀድሞው የኒያላ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ዳሽን ቢራ እና መከላከያ ተጫዋች ዐምና ወደ ደቡብ ፖሊስ አምርቶ መጫወት የቻለ ሲሆን በተለይ በሁለተኛው ዙር ድንቅ ጊዜን ከማሳለፉ ባለፈ ስምንት ግቦችንም ለቢጫ ለባሾቹ አስቆጥሯል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ነገ የሚጀምሩት ሀዋሳ ከተማዎች በቀጣዩ ቀናት ተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ዝውውሮችን ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነና አራት ተጫዋቾችን ከወጣት ቡድኑ እንደሚያሳድጉ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ