ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

አሥራት አባተን በዋና አሰልጣኝ ከቀጠረ በኋላ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ቡታጅራ ከተማ ሁለት ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በዛሬው ዕለትም ክለቡን ከተቀላቀሉት መካከል ፖች አዶል አንዱ ነው። ፖች በመከላከያ እና በቢሾፍቱ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈ ወጣት ጎል ጠባቂ ነው።

ሌላው አዲስ ፈራሚ አብዱልከሪም ቃሲም ነው። የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነው አብዱልከሪም ከዚህ ቀደም በቡራዩ ከተማ፣ አውስኮድ እና አርሲ ነገሌ ተጫውቶ አሳልፏል።

በ2011 የውድድር ዓመት ላለመውረድ የተጫወተው ቡታጅራ ከተማ ዘንድሮ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት ባለፈው ሳምንት የ13 ተጨዋቾችን ውል ከማደሱ በተጨማሪ 6 አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረሙ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ