ሴቶች ዝውውር | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨዋቾችን ማስፈረም ጀምሯል

በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የአሰልጣኛቸውን ውል ካደሱ በኋላ ፊታቸውን ወደ ተጫዋቾች ዝውውር በማድረግ ስድስት ተጨዋቾችን አስፈርመዋል። የአራት ነባሮችንም ውል አድሰዋል።

የመጀመሪያዋ ቡድኑን የተቀላቀለች ተጨዋች ዓለምነሽ ገረመው ናት። ከተከላካይ እስከ አጥቂ በተለያዩ ቦታዎች የመጫወት ክህሎት ያላት ዓለምነሽ ለረጅም ዓመታት በኢትዮ ኤሌክትሪክ አሳልፋለች።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአለምነሽ በተጨማሪ አምስት ወጣት ተጨዋቾችን አስፈርሟል። በዚህም ኝቦኝ የን (አጥቂ)፣ ሳባ ኃይለ ሚካኤል (ተከላካይ)፣ ቅድስት በላቸው (አጥቂ) እና ደመቀች ዳልጋ (አማካይ) ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ እንዲሁም ምህረት ተሰማ (ግብ ጠባቂ) ከጌዲዮ ዲላ አስፈርሟል።

ዘጠኝ ተጨዋቾችን ለመቀነስ ያሰበው ቡድኑ የብዙነሽ ሢሳይ፣ ንግስቲ መዓዛ፣ ሰብለ ቶጋ እና ህይወት ደንጊሶን ውል ማደሱ ተረጋግጧል።


© ሶከር ኢትዮጵያ