የዋልያዎቹ የአሰልጣኞች ቡድን አባላት ባሎኒ የወጣቶች እና ህፃናት ማሰልጠኛ ጎበኙ

ለቻን ማጣርያ በመቐለ ዝግጅት እያደረጉ የሚገኙት የዋልያዎቹ የአሰልጣኞች ቡድን ዛሬ ጠዋት የባሎኒ የህፃናት እና አዋቂዎች የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ጎብኝተዋል።

ዋና አሰልጣኙ አብርሃም መብራቱ፣ ምክትሉ ሙልጌታ ምህረት እና የግብጠባቂዎች አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ እንዲሁም አሰልጣኝ ገብረኪሮስ አማረ የተካፈሉበት ይህ ጉብኝት ለሰልጣኞች የልምድ ልውውጥ እና የተለያዩ ምክሮች የተደረጉበት ነበር።

ባለፈው ዓመት ዋና አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በሃገሪቱ የሚገኙት በርካታ የህፃናት እና ወጣቶች ማሰልጠኛዎች መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ