ሴቶች ዝውውር | መከላከያ ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የቀድሞው የክለቡን ተጫዋች ሰለሞን ታደለን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠረ በኃላ ትላንት አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የነበረው መከላከያ ዛሬ ደግሞ ሦስት በሊጉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ማስፈረሙን አሰልጣኙ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።

ኤደን ሺፈራው መከላከያን የተቀላቀለች ተጫዋች ሆናለች። የቀድሞዋ የደደቢት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቿ የዐምናውን የውድድር ዘመን በአዲስአበባ ከተማ ካሳለፈች በኃላ እመቤት አዲሱን ያጣው መከላከያ ተተኪ በመሆን አምርታለች፡፡

ዘቢብ ኃይለሥላሴ በዛሬው ዕለት ለመከላከያ ፊርማዋን ያኖረች ሌላዋ ተጫዋች ሆናለች፡፡ ከደደቢት ጋር የሊጉን ዋንጫ በተከታታይ ያነሳችው የቀኝ መስመር ተከላካይዋ በ2011 ወደ ንግድ ባንክ አምርታ ተጫውታለች።

ሦስተኛዋ የዛሬ ፈራሚ ጽዮን እስጢፋኖስ ናት። በንግድ ባንክ በመሀል የተከላካይ ቦታ ጠንካራነቷን ያስመሰከረችው ተጫዋቿ ወደ መከላከያ በማምራት የአሰልጣኝ ሰለሞንን ቡድን ተቀላቅላለች፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ