ሲዳማ ቡና ሙሉቀን ታሪኩን አስፈረመ

ሲዳማ ቡና የክለቡ ሦስተኛ ፈራሚ በማድረግ አጥቂው ሙሉቀን ታሪኩን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የፋሲል ከነማ አጥቂ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ስኬታማ ጊዜ በማሳለፍ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ ካስቻሉ ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን በ2011 ወደ አዳማ አምርቶ የነበረ ቢሆንም የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቷል፡፡

አስቀድሞ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ጊትጋት ኮች እና አማካዩ ብርሀኑ አሻሞን በማስፈረም የስምንት ተጫዋቾችንም ውል ያደሰው ክለቡ ዝግጅት ከጀመረ የሰነባበተ ሲሆን በነሀሴ ወር መጨረሻ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ዱባይ ያመራሉ ቢባልም የሚሄዱበት ጊዜ ተራዝሞ በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ ስፍራው የሚያመሩ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ