ቻን 2020| ሦስት ተጫዋቾች የነገው ጨዋታ ያመልጣቸዋል

በቻን ማጣርያ ነገ 10:00 ሩዋንዳን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ ሦስት ተጫዋቾችን በነገው ጨዋታ አይጠቀሙም።

ግብጠባቂው ጀማል ጣሰው በጉዳት ምክንያት የነገው ጨዋታ ሲያመልጠው ሱራፌል ዳኛቸው በካፍ ጨዋታዎች በተመለከታቸው ቢጫዎች ምክንያት ጨዋታው ያመልጠዋል።

ሦስተኛው ጨዋታው የሚያመልጠው ተጫዋች የባህር ዳር ከተማው አማካይ ፍፁም ዓለሙ ሲሆን ያላለቁ የፓስፖርት ጉዳዮች በመኖራቸው የነገው ጨዋታ ያልፈዋል።

በሌላ ዜና ፌዴሬሽኑ የጨዋታውን መግቢያ ይፋ ያደረገ ሲሆን ደረጃ አንድ 100 ብር ፣ ደረጃ ሁለት 50 ብር ፣ ደረጃ ሶስት 25 መሆኑ ተገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ