ቻን 2020| የሩዋንዳው አሰልጣኝ ከጨዋታው አስቀድሞ ሃሳባቸውን ሰጥትዋል

ዛሬ 10:00 በቻን ማጣርያ ኢትዮጵያን የሚገጥሙት የሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን አባላት ላለፉት ሁለት ቀናት በመቐለ ቆይታ ማድረጋቸው ይታወቃል። አሰልጣኙም ትናንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ስለ መቐለ ቆይታቸው እና ቡድናቸው የሚከተለውን አጭር ገለፃ አድርገዋል።

ስለ መቐለ ቆይታቸው

ከዚህ ቀደም ሀዋሳንም አዲስ አበባንም አይቻለው። እዚህ አቀባበሉ ጥሩ ነው። ከኤርፖርት እስከ ሆቴል እና ጥበቃ ያለው ነገር በጣም ጥሩ ነው። አየሩም ፀጥታውም ጥሩ ነው። ጥሩ ዕረፍት ወስደናል። በአጠቃላይ ከጨዋታው በፊት ያለው ዝግጅት ጥሩ ነው።

ስለ ጨዋታው

ከዓለም ዋንጫ ማጣርያው ቡድን ጥቂት ተጫዋቾች ነው የጨመርነው። ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ነው ባይባልም ከሞላ ጎደል መልካም ነው። ከጨዋታው በፊት በኮንጎ የአቋም መለኪያ አድርገናል። በጥሩ ጨዋታም ማሸነፍ ችለናል። እዚህ ግን ሌላ ነገርም ሊፈጠር ይችላል።

ከቡድኑ ምን ይጠበቃል?

የምንጫወትበት መንገድ ምስጢር ነው። የምጫወትበት መንገድ ከነገርኳቹህ ለአሰልጣኛቹ ትነግሩታላቹ።

ስለ ትግራይ ስታዲየም

ስቴድየሙ ጥሩ ነው፤ መጫወቻ ሜዳውም ጥሩ ነው። የቀሩት ነገሮች ተጠናቀው ከዚህ በበለጠ አሪፍ ይሆናል ብዬ እጠብቃለሁ። በኢትዮጵያ ጥሩ ተጫዋቾች አሉ። ስቴድየሙን ተረባርባችሁ መጨረስ አለባችሁ።


© ሶከር ኢትዮጵያ