ወላይታ ድቻ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል

የጦና ንቦቹ እድሪስ ሰዒድን የክለቡ አምስተኛ ፈራሚ በማድረግ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በዓምናው የውድድር ዘመን በትውልድ ከተማው ክለብ ወሎ ኮምቦልቻ ሲጫወት የቆየው ይህ ተጫዋች 2006 ወልዲያ፣ በ2009 ደግሞ መቐለ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድጉ የክለቡ ስብስብ ውስጥ ጉልህ ሚና ነበረው። በአውስኮድ እና ጥቁር ዓባይ የተጫወተው እድሪስ ቀጣይ ማረፊያውን ወላይታ ድቻን በሁለት ዓመት ውል አድርጓል፡፡

ወላይታ ድቻ የእድሪስን ጨምሮ የአምስት ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም ከተስፋ ቡድኑ ደግሞ አምስት ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል።


© ሶከር ኢትዮጵያ