ስሑል ሽረ የአይቮሪኮስታዊውን አጥቂ ውል አራዝሟል

በሁለተኛው ዙር ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ አስደናቂ ቆይታ ያደረገው ሳሊፍ ፎፋና በክለቡ የሚያቆየውን ውል አድሷል።

ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በሲዳማ ቡና የሙከራ ጊዜን አሳልፎ በክለቡ የመያዝ ዕድሉ በመጥበቡ ወደ ስሑል ሽረ ካመራ በኋላ ባሳለፈው የሙከራ ጊዜ አሰልጣኙን በማሳመኑ በስድስት ወራት ክለቡን ተቀላቅሎ 11 ግቦችን በማስቆጠር ክለቡ በሊጉ እንዲቆይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

የቀድሞው አል-ሃላሙራ፣ አፍሪካን ስፖርትስ እና ማንጋ ስፖርት አጥቂ ያዝነው ዓመት እስኪጠናቀቅ ድረስ በቢጫ እና አረንጓዴ ለባሾቹ ቤት ቆይታ የሚኖረው ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ