ታንዛንያ የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ አሸናፊ ሆነች

ኢትዮጵያን ጨምሮ አስራ አንድ ሃገራት የተሳተፉበትና ዩጋንዳ ያዘጋጀችው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬ ሲጠናቀቅ ታንዛንያ ኬንያን በማሸነፍ ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች።

በግማሽ ፍፃሜው ኤርትራን እና ሱዳንን አሸንፈው ወደ ፍፃሜው የደረሱት ታንዛኒያ እና ኬንያ ቀደም ብሎ እኩል የዋንጫ ግምት እንደተሰጣቸው ሲታወስ በዛሬው ጨዋታም የተጠበቀው ፉክክር ተስተናግዶ ታንዛንያ ጆን ኦቲኖ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ጨዋታውን 1-0 አሸንፋለች።

ቀደም ብሎ በተከናወነው የደረጃ ጨዋታ ኤርትራ ሱዳንን 1-0 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

በውድድሩ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ውጭ በዋና ዳኛ ለሚ ንጉሴ እና ረዳት ዳኛ በላቸው ይታየው የተወከለችው ኢትዮጵያ አንድ ግብ በማስቆጠር አስር ግቦች አስተናግዳ ከውድድሩ በደካማ ውጤት መሰናበቷ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ