ደቡብ ፖሊስ ሀይማኖት ወርቁን አስፈረመ

የተከላካይ አማካዩ ሀይማኖት ወርቁ ለደቡብ ፖሊስ ዛሬ ፊርማውን አኑሯል፡፡
በትውልድ ከተማው ባህር ዳር እግር ኳስን በመጫወት የጀመረው የመሀል አማካዩ በከተማው ሌላኛው ክለብ አውስኮድ ከተጫወተ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር ስኬታማ የከፍተኛ ሊግ ቆይታን በማድረግ ወደ ሀዋሳ ከተማ አምርቷል። በ2010 ወደ ወላይታ ድቻ ተጉዞ በፕሪምየር ሊጉ እና በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይ ቡድኑ ስኬታማ ጉዞን እንዲያደርግ ካስቻለ በኋላ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት የተመስገን ዳናውን ክለብ መቀላቀል ችሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ