ሰበር ዜና | የ2012 ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ታወቀ

የፕሪምየር ሊጉ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበትን ቀን ወስኗል።

የመጀመርያቸው በሆነው በዚህ ስብሰባ ሁሉም የኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ስብሰባቸው ከወሰኑት ውሳኔ መካከል የ2012 የፕሪምየር ሊግ ከኀዳር 6 እና 7 ቀን እንዲጀምር መወሰኑን የኮሚቴው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ቦታ እና ቀን በቅርቡ ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዝርዝር የስብሰባውን ውሎ ከቆይታ በኃላ እንመለስበታለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ