ወልቂጤ ከተማ ቶጓዊውን አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

ቶጓዊው አጥቂ ጃኮ አራፋት ለወልቂጤ ከተማ ለመጫወት ከስምምነት ደርሷል፡፡

ከሀገሩ ቶጎ ክለብ ሜሬላ እግርኳስን ጀመረውና የሩሲያው አንዚ ማካቻካላን ጨምሮ በዓለም ዙርያ ለአስራ ስድስት ክለቦች መጫወት የቻለው ይህ የቀድሞው የቶጎ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የጋቦኑን ሞናና ከለቀቀ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በ2009 በመምጣት በሀዋሳ ከተማ የተሳካ ዓመትን በማሳለፍ በግሉ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ ውስጥ ተፎካካሪ በመሆን ዓመቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በ2010 ወደ ወላይታ ድቻ ካመራ በኋላ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ መልካም የውድድር ጊዜን ማሳለፍ ቢችልም በፕሪምየር ሊጉ ግን በሀዋሳ ያሳየውን አቋም መድገም ያልቻለው አንጋፋው አጥቂ በ2011 የውድድር ዓመት በባህርዳር ከተማ ቆይታን ያደረገ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ቆይታው አራተኛ ክለቡ የሆነው ወልቂጤ ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ