ድሬዳዋ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ተጫዋቾችን በሙከራ እየተመለከተ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፉት ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ ባሳለፉት ሙከራ ጊዜ አሰልጣኝ ስምዖን ዓባይ ማሳመን የቻሉት ሦስት የድሬዳዋ ፖሊስ ተጫዋቾች ናቸው ክለቡን መቀላቀል የቻሉት። የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ከድር አዩብ፣ የመስመር አጥቂው ፈርዓን ሰዒድ እና አጥቂው ሳሙኤል ዘሪሁን ክለቡን ዛሬ በይፋ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

እስከ አሁን በድምሩ አስራ ሁለት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ድሬዳዋ ከተማዎች ነገ ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርሙ ይጠበቃል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ