መከላከያ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች መለያየት ጀምሯል

መከላከያ ከሦስት ተጫዋቾች መለያየቱ ሲረጋገጥ በቀጣይ ቀናትም ከሌሎች ተጫዋቾች ይለያያል ተብሎ ይጠበቃል።

የፕሪምየር ሊጉ ፎርማት ወደ 24 ቡድኖች ማደጉ ተከትሎ በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት መከላከያዎች ቀጣይ ዓመት በከፍተኛ ሊግ እንደሚሳተፉ ከተረጋገጠ በኃላ በክረምቱ ካስፈረማቸው በርካታ ተጫዋቾች መለያየት ጀምረዋል። ቀድመው ከክለቡ ጋር የተለያዩት በዚ ዝውውር መስኮት ከድሬዳዋ ቡድኑን የተቀላቀለው አንተነህ ተስፋዬ፣ ከሃዋሳ ከተማ ወድ ቡድኑ የተዘዋወረው ፍቅረየሱስ ተ/ማርያም እና ከሲዳማ ጋር ጥሩ ዓመት አሳልፎ የጦሩን ቤት የተቀላቀለው ሃብታሙ ገዛኸኝ ናቸው።

መከላከያ በቀጣይ ቀናትም ከሌሎች ተጫዋቾች ይለያያል ተብሎ ሲጠበቅ በነሱ ምትክም በስፋት ወደ ገበያው ይወጣል ተብሎ ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ