የትግራይ ዋንጫ ይካሄዳል

የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ የነበረው የትግራይ ዋንጫ እንደሚካሄድ ሲረጋገጥ የውድድሩ ዝርዝር በቀጣይ ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ባለፈው የውድድር ዓመት መጀመርያ በሽቶ ሚድያ እና ኮሙኒኬሽን እና በትግራይ ወጣቶች ጉዳይ እና ስፖርት ፅህፈት ቤት ለመጀመርያ ጊዜ የተካሄደው የትግራይ ክልል ዋንጫ ዘንድሮ በተለያየዩ ምክንያቶች የመካሄዱ ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም በሁለቱም አዘጋጆች በተደረሰ ስምምነት ለሁለተኛ ዓመት እንዲካሄድ ተወስኗል።

በመጀመርያው ውድድሩ ተጋባዦቹ ድሬዳዋ ከተማዎችን ጨምሮ ስድስት ክለቦች ያሳተፈው ይህ ውድድር በዘንድሮው ውድድር ስንት ክለቦች እንደሚሳተፉበት ያልተረጋገጠ ሲሆን ይህንና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች አስመልክተውም አዘጋጆቹ በቀጣይ ቀናት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ በተካሄደው ውድድር መቐለ 70 እንደርታ በፍፃሜው ድሬዳዋ ከተማን አሸንፎ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ