ጅማ አባጅፋር ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

ጋናዊው ግዙፍ አጥቂ ያኩቡ መሀመድ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል የጅማ አባጅፋር ተጫዋች ሆኗል፡፡

በአራት የተለያዩ ሀገራት ባሉ ክለቦች ውስጥ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወቱን ያሳለፈው ይህ ግዙፍ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በሀገሩ ጋና ለአሳንቲ ኮቶኮ፣ አሳንቲ ጎልድ እና ኤልሚና ለተባሉ ክለቦች መጫወት የቻለ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ማርቲዝበርግ፣ ለሞሮኮው ዩኒየን ኤይት እና ለኃያሉ ራጃ ካዛብላንካ ተጫውቷል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ለኢኳቶሪያል ጊኒው ክለብ ፉቱሮ ኪንግ ሲጫወት ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የጅማ አባጅፋር ሦስተኛ የውጪ ዜጋ ፈራሚ በመሆን ቡድኑን በይፋ መቀላቀል ችሏል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ