ጅማ አባጅፋር ተጨማሪ ተጫዋች አስፈረመ

ወንድማገኝ ማርቆስ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል፡፡

ባለፈው ውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊግ ለጅማ አባ ቡና በመጫወት ያሳለፈው ተጫዋቹ በዋናነት በተከላካይ ቦታ እና እንዲሁም ደግሞ በአማካይ ተከላካይነት መጫወት የሚችል ሲሆን በአሰልጣኙ የተሰጠውን የሙከራ ጊዜ በአግባቡ በመወጣቱ ክለቡን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡

በርካታ የውጪ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው የአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ቡድን በዛሬው ዕለት ሁለት ጋናዊ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ