ከፍተኛ ሊግ | የካ ክፍለ ከተማ ስድስት ተጫዋቸችን አስፈረመ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ የሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ ስድስት አዳዲስ ተጫዎቾች ሲያስፈርም የአንድ ነባር ተጫዋች ውል አድሷል።

በግብ ጠባቂ ስፍራላይ አስግድ ታምሬ ከኢኮስኮ እና አዲሱ ቦቄ ከከፋ ቡና ሲፈርሙ በተከላካይ መስመር ሳሙኤል አስፍሬ ከአረካ ከተማ፣ በአማካይ ስፍራ ላይ አዳነ አየለ እና ሚኪያስ አምሀ ከሺንሺቾ ወደ ቡድኑ ተቀላቅለዋል። በተያያዘም አማካዩ ዮናስ ሰለሞን ለተጨማሪ አመት በክለቡ የሚያቆየውን ውል አድሷል።

የካ ከዚህ ቀደም ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሞ የስምንት ነባሮች እና የአሰልጣኝ ባንተይርጋ ጌታቸውን ውል ማደሱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ