ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአዲሱ አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ እየተመራ ዝግጅቱን በባቱ ከተማ እያደረገ ያለው ሻሸመኔ ከተማ ሰባት ተጫዋቾች ማስፈረም ችሏል።

በተከላካይ ስፍራ ላይ ፍሬዘር መንግስቱ ከሱሉልታ ከተማ፣ ተመስገን ሽብሩ ከባቱ ከተማ እና አካሉ አበራ ከአርባ ምንጭ ሲፈርሙ አማካይ ስፍራ ላይ ቃልአብ ጋሻው ከበቡራዩ ከተማ አሰልጣኙን ተከትሎ ቡድኑን ተቀላቅሏል። በቀኝ መስመር ላይ የሚጫወተው ሱራፌል አየለ ከለገጣፎ ለገዳዲ እና በሁለቱም ክንፎች መጫወት የሚችለው አሸናፊ ጥሩነህ ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን እንዲሁም አጥቂው ኤርምያስ ዳንኤል ከኢትዮጵያ መድን ወደ ሻሸመኔ ያመሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ቡድኑ በቅርቡ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ የሚቀላቅል መሆኑን ገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ