ፌዴሬሽኑ ለአዳማ ከተማ በገደብ የተቀመጠ መመርያ ላከ

ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተጫዋቾች ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በገደብ የተቀመጠ መመርያ በደብዳቤ ለክለቡ ልኳል።

አዳማ ለ24 ተጫዋቾቹ የወራት ደሞዝ ያልከፈለ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ ይስጠን በማለት ዛሬ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብተዋል። በዚህም መሠረት የቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ክለቡ ከጥቅምት 21–ኀዳር 2 ቀን ድረስ ምላሽ እንዲሰጥ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ደብዳቤ ልኳል።

በተቀመጠው ቀነ ገደብ ክለቡ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በተደነገገው አንቀፅ መሠረት በቀረበለት አቤቱታ መነሻነት ውሳኔ የሚያስተላልፍ መሆኑን አሳውቋል።

የደብዳቤው ሙሉ ሀሳብ


© ሶከር ኢትዮጵያ