አራት ኢትዮጵያውያን ሴት ዳኛች ወደ ታንዛንያ ያመራሉ

ከኅዳር 3 እስከ 13 በታንዛንያ በሚካሄደው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ላይ ለመዳኘት ከኢትዮጵያ ሁለት ዋና እና ሁለት ረዳት ዳኞች ተመርጠዋል።

ወደ ስፍራው የሚያመሩት ዋና ዳኞች ፀሐይነሽ አበበ እና አስናቀች ገብሬ (ፎቶ ከላይ) እና ረዳት ዳኞች ወይንሸት አበራ እና ወጋየሁ ዘውዴ (ፎቶ ከታች) ናቸው።

ረዳት ዳኞች የሆኑት ወይንሸት አበራ እና ወጋየሁ ዘውዴ ከዚህ በፊት በተካሄዱ የሴካፋ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ወይንሸት ከሁለት ዓመት በፊት በተደረገው፤ ወጋየሁ ደግሞ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ውድድር ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል። ወደ ውድድሩ በዋና ዳኝነት የሚያመሩት ፀሐይነሽ አበበ እና አስናቀች ገብሬ ደግሞ የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ውድድራቸው የሚመሩ ይሆናል።


በሴካፋ ውድድሮች ተሳትፏቸው እየጨመረ የመጣው ኢትዮጵያውያን ዳኞች ከዚህ ቀደም በሁለት የሴካፋ የወንዶች ውድድሮች በለሚ ንጉሴ ፣ ብሩክ የማነ ብርሃን እና በላይ ታደሰ መወከላቸው ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ