ሲዳማ ቡና በትግራይ ዋንጫ ላይ ይሳተፋል

ሲዳማ ቡና በዚህ ወር መጨረሻ በሚካሄደው የትግራይ ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፍ ተረጋገጠ

በሽቶ ሚድያ እና ኮምኒኬሽን፣ ትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዲሁም የትግራይ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጥምረት የሚካሄደው ይህ ውድድር ጥቅምት 30 የሚጀመር ሲሆን በቀጣይ ቀናት ሙሉ ተሳታፊዎች ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል። ሐሙስ ጥቅምት 20 በሚጀምረው የደቡብ ሠላም ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፍ ሲጠበቅ የነበረው ሲዳማ ቡናም በዚህ ውድድር ላይ እንደሚካፈል ተረጋግጧል።

ውድድሩ እስካሁን ድረስ መቐለ 70 እንደርታ ፣ ስሑል ሽረ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ደደቢት ፣ አክሱም ከተማ እና ሶሎዳ ዓድዋ እንደሚሳተፉበት ሲረጋገጥ አዳማ ከተማም ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ