ካሜሩን 2021 | ዋልያዎቹ የማጣርያ ጨዋታዎቻቸውን የሚያደርጉባቸው ቀናት ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት ጋር በተከታታይ ይጫወታል፡፡

ቡድኑ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ አንታናናሪቮ ላይ ኅዳር 6 ማዳጋስካርን የሚገጥም ሲሆን ከሦስት ቀናት በኃላ ማለትም ህዳር 9 በመቐለ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጠንካራው የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድንን በሜዳው ይገጥማል፡፡

በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ በትላንትናው ዕለት ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረገ ሲሆን የፊታችን ሰኞ በትግራይ ስታዲየም የማጣርያ ዝግጅቱን የሚጀምር ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ