ወላይታ ድቻ በትግራይ ዋንጫ ላይ ይሳተፋል

በደቡብ ሠላም ዋንጫ ይሳተፋሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ወላይታ ድቻዎች በትግራይ ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።

በሽቶ ሚድያ እና ኮምኒኬሽን፣ ትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የትግራይ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጥምረት የሚካሄደው ይህ ውድድር ጥቅምት 30 የሚጀመር ሲሆን ከወላይታ ድቻ በተጨማሪ ሲዳማ ቡናም እንደሚሳተፍ መገለፁ ይታወቃል። ከሁለቱ ተጋባዥ ቡድኖች በተጨማሪ የፕሪምየር ሊጎቹ መቐለ 70 እንደርታ እና ስሑል ሽረ እንዲሁም የከፍተኛ ሊጎቹ ደደቢት፣ አክሱም ከተማ እና ሶሎዳ ዓድዋ በውድድሩ እንደሚሳተፉ ያረጋገጡ ቡድኖች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ