በ2019/20 ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ከኢትዮጵያ የሚወከሉ ኮሚሽነሮች ታወቁ

በያዝነው የ2019/20 የውድድር ዘመን የሚደረጉ የአህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ውድድሮች ላይ ከኢትዮጵያ የሚሳተፉ ኮሚሽነሮች ተለይተዋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መስፈርት በማውጣት በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የሚወክሉ አራት የውድድር ታዛቢዎች (ኮሚሽነሮች) አወዳድሮ ለመምረጥ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ለሦስት ቀን የተሰጠውን ፈተና ከወሰዱ በኃላ ሰለሞን ገብረሥላሴ እና ግዛቴ ዓለሙ በወንዶች ሲመረጡ ተስፋነሽ ወረታ እና ሳራ ሰዒድ በሴቶች ተመርጠዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ