የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ሉሲዎቹን አበረታቱ

ሉሲዎቹ የአቋም መለኪያ ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት ወቅት የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በስታዲየም በመገኘት አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከወጣቶች አካዳሚ ከ15 ዓመት በታች ታዳጊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስቴዲየም በሚያደርገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ላይ ነው ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና ዶ/ር ሂሩት ካሳ (የባህልና ቱሪዚም ሚኒስትር) የተገኙት። በጨዋታው እረፍት ሰዓት ላይ ክብርት ፕሬዝደንቷ ተጫዋቾች በማበረታታት የማነቃቂያ ንግግር አድርገዋል።

በማስከተልም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የኦሊምፒክ ፕሬዝደንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ለክብርት ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ሙሉ ቱታ አበርክተውላቸዋል።

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ኀዳር ወር በሚጀምረው የሴካፋ ዋንጫ ላይ እንደሚሳተፍ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ