ወልዋሎዎች የሚሳተፉበት ውድድር ታውቋል

በሁለት የቅድመ ውድድር ዝግጅቶች ምድብ ድልድል የተካተቱት ወልዋሎዎች በየትኛው ውድድር እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን የቀረበላቸው ግብዣ ተቀብለው በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለመሳተፍ የወሰኑት ቢጫ ለባሾቹ በትናንትናው ዕለት በትግራይ ዋንጫ የምድብ ድልድል መካተታቸው ተከትሎ ክለቡ በየትኛው ውድድር ይሳተፋል የሚለው ጥያቄ ከበርካቶች ተነስቷል።

ሆኖም በሁለቱም ውድድሮች ምድብ ድልድል ውስጥ የገቡት ወልዋሎዎች በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እንደሚሳተፉ እና ለውድድሩ ጥሩ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ቡድን መሪው ሃዲ ሰዊ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። “በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ልምምድ እየሰራን ለውድድሩ በጥሩ ዝግጅት ነው የምንገኘው ፤ መጀመርያ ውድድሩ ውድድሩ እንደማይካሄድ ስለተነገረ ነው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ግብዣ ተቀብለን የመጣነው እዚ ለ አስራ አራት ቀናት ስንዘጋጅም በይፋዊ መንገድ ለውድድሩ እንድንሳተፍ ጥያቄ ያቀረበልን የለም ” ብለዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ