የዋልያዎቹ እና ዝሆኖቹን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት የሚያደርጉን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የሚመሩት አራት ሞዛምቢካውያን ዳኞች ባህርዳር ገብተዋል።

ዋናው ዳኛ ዘካርያስ ሆራሲዮ፣ ረዳት ዳኞች ሴልሶ አርሚንዶ እና አርሲኒዮ ቻድሪክዊ እንዲሁም አራተኛ ዳኛ ዘፋንያስ ቸሚላ ጨዋታውን ለመምራት በካፍ የተመረጡ ዳኞች ናቸው።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታቸው ወደ አናታናናሪቮ አምርተው በጠባብ ውጤት ተሸንፈው ዛሬ ወደ ባህር ዳር ከተማ የገቡት ዋልያዎቹ በዛሬው ዕለት ቀለል ያለ ልምምድ ያደረጉ ሲሆን በአንፃሩ ዝሆኖቹ በባህር ዳር ከአንድ ቀን የዘለለ ቆይታ ሳያደርጉ እና ከጨዋታው ቀደም ብለው ልምምድ ሳይሰሩ ጨዋታውን እንደሚያካሂዱ ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዜና ከኢትዮጵያ ጋር በምድብ ‘ K ‘ የተደለደሉት ኒጀር እና ማዳጋስካር ነገ በአንድ ሰዓት በኒጀር ስታደ ሰይኒ ኮይንትቼ ይገናኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ