ዋልያዎቹ አራት ተጨዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል

ከሰዓታት በፊት ወደ ባህር ዳር ያቀኑት ዋሊያዎቹ ለተጨማሪ ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው ታውቋል።
ወደ ማዳካስካር ካቀናው የልዑካን ስብስብ ዛሬ ባህር ዳር ላይ ቡድኑን የተቀላቀሉት ዮናስ በርታ፣ መሳይ ጳውሎስ፣ ተክለማርያም ሻንቆ እና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው። 

አራቱ ተጨዋቾች ከዚህ ቀደም ከአሰልጣኙ ጥሪ የቀረበላቸው ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ተቀንሰው ወደ ማዳጋስካር ሳያቀኑ መቅረታቸው ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ