የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን ታውቋል

በመቐለ 70 እንድርታ እና በፋሲል ከነማ መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ የሚካሄድበት ጊዜ ታውቋል።

በ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው መቐለ 70 እንድርታ እና በኢትዮጵያ ጥሎማለፍ ዋንጫ አሸናፊ ፋሲል ከነማ መካከል የሚደረገው የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ኅዳር 16 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረግ ተሰምቷል።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ቀደም ብሎ ጥቅምት 23 ሊደረግ እንደነበር የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ