ዋሊያዎቹ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ትላንት ባህር ዳር ላይ ኮትዲቯርን ያሸነፉት ዋሊያዎቹ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ትላንት ጨዋታው ከተደረገበት ባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከአንድ ሰዓታት በፊት ያመራው ቡድኑ ቦሌ አየር ማረፊያ ደርሶ ደማቅ አቀባበል ከተደረገለት በኋላ በቀጥታ ወደ ጁፒተር ሆቴል በማምራት እረፍት አድርጓል። በአሁኑ ሰዓት ምሳ እየተመገቡ የሚገኙት ተጨዋቾቹ ከደቂቃዎች በኋላ በፌደሬሽኑ ሽልማት ሊበረከትላቸው እንደሆነ ሰምተናል።

በስካይ ላይት ሆቴል በሚደረገው የሽልማት ስነ-ስርዓት የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት እነወደሚገኙ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ